Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካን እንቅስቃሴ መስራችና የአፍሪካ  ህብረት መቀመጫ ናት-ፕ/ት ኢስማኤል ኡመርጌሌህ

አዲስ አበበ፣ መስከረም 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅቡቲው ፕሬዚደንት ኢስማኤል ኡመርጌሌህ በዚህ ልዩ በሆነ ቀን እዚህ በመገኘቴ  ክብር ይሰማኛል ብለዋል።

በዚህም ለወንድሜ   ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ  እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ ብለዋል።

አያይዘውም ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ህብረት ያበረከተችውን እና ያላትን ድጋፍ እና ክብር አድንቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካን እንቅስቃሴ መስራችና የአፍሪካ  ህብረት መቀመጫ ናት ብለዋል።

ኢትዮጵያ በታሪኳ ብዙ ችግሮች ቢያጋጥሟትም የሚገጥማትን ፈተና ሁሉ በራሷ መንገድ ትፈታቸዋለች ፡፡  አሁንም ጠንካራ ሀገር ሆና ቀጥላለች ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያ ለዘለዓለምም ትኑርም ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

Exit mobile version