Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በማዕከላዊ አየር ምድብ በሥራ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የሠራዊት አባላት የማዕረግ እድገት ተሠጠ

አዲስ አበባ፣መስከረም፣25፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል በማዕከላዊ አየር ምድብ በሥራ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ እና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ የምድቡ የሠራዊት አባላት የማዕረግ እድገት ሠጠ፡፡

የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለሎጂስቲክ ብርጋዴር ጀነራል ነገራ ለሊሳ÷ አሸባሪው ቡድን የፈፀመውን ወረራ በመቀልበስ ረገድ አየር ኃይላችን ከፍተኛ ጀግንነት እየፈፀመ መሆኑን ተናግረዋል።

ለዘመቻው ስኬታማነት ማዕከላዊ አየር ምድብ ያበረከተው እና እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ የሚያስደንቅ ነው ብለዋል ፡፡

የማዕከላዊ አየር ምድብ አዛዥ ኮሎኔል ወንዱ ኬዳ በበኩላቸው÷ አየር ምድቡ ህውሓት በሠሜን ዕዝ እና በሠሜን አየር ምድብ ብሎም በአማራ ክልል እና በአፋር ክልል የፈፀመውን ወረራ በመቀልበስ ዘመቻ አኩሪ ድል እያስመዘገበ መሆኑን አውስተዋል፡፡

ተሿሚዎች የማዕረግ ሹመቱ በአሸባሪው የህውሓት ቡድን ላይ የተጀመረውን ዘመቻ አጠናክረን እንድንቀጥል ትልቅ መነቃቃት ይፈጥርልናል ማለታቸወን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገፅ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version