Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ምክር ቤቱ ከጧቱ 3:30 ጀምሮ ልዩ ስብሰባውን ያካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ አመት 1ኛ ልዩ ስብሰባውን ነገ ከጧቱ 3:30 ጀምሮ ያካሄዳል።
ም/ቤቱ በልዩ ስብሰባው የኢፌዴሪ ኘሬዘዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ/ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ም/ቤቶች የጋራ መደበኛ ስብሰባ ያቀረቡትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን ያደምጣል።
በተጨማሪም የፌዴራል መንግስት የአስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባርን መወሰኛ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያፀድቃል።
በመጨረሻም የሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ በማጽደቅ የእለቱን ልዩ ስብሰባ ያጠናቅቃል።
ልዬ ስብሰባውን ነገ ከጧቱ 3:30 በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በዋናው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል።
ምንጭ፡- ምክር ቤቱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version