አዲስ አበባ፣መስከረም፣25፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቀጠናዊ ዲፕሎማሲ እና ባለ ብዙ ወገን ትብብር ላይ የተጀመሩ ስራዎችን ልታጎለብት እንደሚገባ ምሁራን ተናገሩ ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ሱራፌል ጌታሁን ÷ኢትዮጵያ በቀጠናዉ ያላትን የጋራ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በዲፕሎማሲዉ መስክ አዳዲስ አሰራሮችን ገቢራዊ ማድረግ እንደሚገባት ተናግረዋል ፡፡
ቀጠናዊ ትብብርን ማጎልበት የምዕራባዉያኑን ዲፕሎማሲያዊ ጫና በመመከት ረገድ ያለዉ ሚና ከፍ ያለ እንደሆነ ያብራሩት አቶ ሱራፌል ፤የአፍሪካ ሃገራት ምጣኔ ሃብታዊ ትብብር ላይ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባም አንስተዋል፡፡
አንጋፋዉ የታሪክና ባህል ተመራማሪ ረዳት ፕሮፌሰር አህመድ ዘከርያ በበኩላቸዉ ÷ኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብን የመሰሉ ፕርጀክቶቿ ቀጠናዊ ትስስርን በተጨባጭ ለማሳደግ እንደሚያግዛት አስረድተዋል ፡፡
ወደብን በጋራ ለማልማት ፣ በትራንስፖርትና ሎጅስቲክ፣ ባህልና ቱሪዝም ፣ ንግድና ምጣኔ ሃብት ትስስርን ከፍ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል ፡፡
ምሁራኑ ጎረቤት የአፍሪካ ሃገራት ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ ጠንካራ ስራዎችን ለመስራት ያሳዩት መነሳሳት ጉልበት የሚሰጥ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡
በአወል አበራ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!