Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች አልጋወራሽ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች አልጋወራሽ ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ነኸያን ጋር በስልክ ተወያይተዋል።

በውይይታቸው በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የወዳጅነትና የትብብር ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም በጋራ እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን የኤሚሬት ዜና ወኪል ዘግቧል፡፡

መሃመድ ቢን ዛይድ አል ነኸያን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በድጋሚ በመመረጣቸውም የእንኳን ደስ አሎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version