አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲሱ የመንግስት ምስረታ የትምህርት ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከቀድሞ የትምህርት ሚኒስትር ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡
ለአዲሱ ሚኒስትርም የቀድሞ የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ለሚኒስትሩ ስለ ትምህርት ሚኒስቴር አደረጃጀትና እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች እንዲሁም ወደፊት የታቀዱ እቅዶች በዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
ፕሮፌሰር ብርሃኑ የትምህርት ሚኒስቴር ሀገሪቱ በርካታ ስራ ከምትጠብቅባቸው ዘርፎች አንዱ መሆኑን ጠቁመው÷ ትውልድን ሊቀይር የሚችል ስራ ለመስራት የቻሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡
ካለው አመራርና ሰራተኛ ጋር በመወያየት ስራዎችን እንደሚሰሩ ገልጸው÷ ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!