አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከጎግልና “አፍሪካ 118” ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር የቦታ መገኛን በጎግል ካርታ ውስጥ ለመመዝገብ የሚያስችል ስልጠና ለክልል የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተቋማት ባለሙያዎች እየሰጠ ነው።
ስልጠናው በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ተቋማትን የመገኛ ቦታዎች በጎግል ካርታ ውስጥ በማካተት ሰዎች በቀላሉ ፈልገው እንዲያገኟቸው ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል፡፡
የቦታ መገኛ ምዝገባው በኢኮሜርስ ግብይት የተፈፀመባቸውን እቃዎች ለደንበኞች ባሉበት ቦታ ለማድረስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል።
የዲጂታል አድራሻ ምዝገባ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት አንዱ ቁልፍ ስራ መሆኑን በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ፅህፈት ቤት ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር አብዮት ባዩ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና ድርጅቶች የሚገኙበትን ቦታ የመመዝገብ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያነሱት ዳይሬክተር ጀነራሉ÷ ይህንን ለማድረግ የሚያስችሉ ተከታታይ ስልጠናዎች ለባለሙያዎች ይሰጣል ብለዋል።
በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች እና ጤና ተቋማት በጎግል ካርታ ውስጥ የመመዝገብ ስራ መጠናቁን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share