Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ የገጠሟትን ፈተናዎች ለመሻገር የአዲሱ ካቢኔ አባላት በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት መስራት አለባቸው – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከውስጥም ሆነ ከውጭ የገጠሟትን ፈተናዎች ለመሻገር የአዲሱ ካቢኔ አባላት በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት መስራት አለባቸው ሲሉ ምሁራን ተናገሩ፡፡

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ የነበራቸው የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ የመንግስትና የህዘብ አስተዳደር ተመራማሪ ዶክተር መሀመድ አሊ ÷ ሀገርን የማገልገል መመሪያን የተቀበሉት ሚኒስትሮቹ ኢትዮጵያ ያለችበት ፈታኝ ወቅታዊ ሁኔታን ያገናዘበ ስራን መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል ።

የፖለቲካ ፤ የኢኮኖሚም ሆነ ማህበራዊ ተግዳሮቶችን ለመወጣት ግን ከሌብነት የጸዳ እና ከብሄር ጥገኝነት የተላቀቀ ስራ መስራት አለባቸው ብለዋል ።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህሩ አቶ ሀይሉ ነጋ ÷ አለም አቀፋዊው የዲፕሎማሲ ጫናን አዲሱ ካቢኔ ትኩረት ሊሰጠው ከሚገቡ የቤት ስራዎች መካከል ናቸው ይላሉ።

የሰላምና ደህንነት አማካሪውን ዶክተር መሳይ ሀጎስ በበኩላቸው÷ ብዝሃ ሀሳብ የሚስተናገድበት የሚኒስትሮች ምክር ቤትም ለዲሞክራሲው ባህል ማደግም ሆነ ችግሮችን ለመፍታት ጎልህ ሚናን ይወጣል ብለዋል ።

በዜጎች ድምጽ የተመሰረተው የአዲሱ መንግስት ካቢኔ አባላት ከህዝቡ የተሰጣቸውን ሀላፊነት በአግባቡ በመወጣት ሀገርን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ማሻገር እንዳለባቸው ተናግረዋል ።

በሀይለየሱስ መኮንን

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version