አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጣት ምህረታብ ሙሉጌታ በአፋር ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ለአፋር ልዩ ሀይልና ሚሊሻ አባላት የግማሽ ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉን ለአፋር ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባ አስረክቧል።
ከዚህ ቀደም ለመከላከያ ሰራዊት የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ያደረገው ምህረታብ፣ ድጋፉን ያደረኩት ሌሎች እንዲነሳሱ የተፈናቀሉትን ወገኖች እና የፀጥታ ሀይሉን ከጎናችሁ ነን ለማለት ያህል ነው ብሏል።
ሀገር ከባድ ፈተና ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ጊዜ ድጋፍ ማድረግ ከሁሉም የሚጠበቅ ነው ያለው ምህረታብ ሙሉጌታ ፣ ሁላችንም የቻልነውን ማድረግ አለብን የተፈናቃይ ወገኖችን እምባ ልናብስም የግድ ይለናል ብሏል።
በአፋር ህዝብና መንግስት ስም ምስጋና ያቀረቡት አቶ አወል አርባ፣ እውነተኛ ወዳጆቻችንን በምንለይበት ጊዜ ኢትዮጵያውያን እርስ በእርስ መደረሳችን እጅጉን አስፈላጊ ነው ብለዋል።
የምህረታብ ድጋፍ ለሌሎች ኢትዮጵያውን የሚያስተምር እና በግለሰብ ደረጃ ኢትዮጵያን የመታደግ ሚናን ሁሉም እንዲወጣ የሚያነሳሳ ነው ብለዋል አቶ አወል አርባ።
በሀብታሙ ተ/ስላሴ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!