አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ የስራ ዕድል የተፈጠረላት ሰሚራ መሀመድ በዛሬው ዕለት መኖሪያ ቤት ተሰጥቷታል፡፡
ቤተሰቦቿ፣ አመራሮችና የአስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት ነው የቁልፍ ርክክብ ስነ ስርዓቱ የተከናወነው፡፡
የመኖሪያ ቤት ቁልፉን ያስረከቡት የንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ነጻነት ዳባ ናቸው፡፡
አስተዳደሩ ለሰሚራ የሚያደርገውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል ሥራ አስፈጻሚዋ፡፡
ሰሚራ ተገቢውን እንክብካቤ እና የህግ ድጋፍ እንድታገኝ ላደረጉ አካላትም ወይዘሮ ነጻነት ዳባ ምስጋና ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!