Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጥቅምት ወር የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የጥቅምት ወር የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል ንግድና ቀጠናዊ ትስስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የሁሉም ነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ መስከረም ወር በነበረበት እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡
ነገር ግን የአውሮፕላን ነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ መስከረም ወር አንድ ሊትር ሲሸጥበት ከነበረው 45 ብር ከ76ሳ ወደ 47 ብር ከ43ሳ ከፍ እንዲል የተወሰነ መሆኑ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩልም በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግ የሚችል መሆኑ ታውቋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version