Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29 ፣2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ በማታና በርቀት ትምህርት መርሐ ግብር ያስተማራቸውን 6 ሺህ 163 የቅድመ ምረቃና ድሕረ ምረቃ ተማሪዎችን በወዳጅነት አደባባይ እያስመረቀ ነው።
ከተመራቂዎቹ መካከል 155 የሶስተኛ ዲግሪ ዕጩ ምሩቃን ናቸው።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
ከተመራቂዎቹ መካከል 2 ሺህ 559 ድሕረ ምረቃ፣ 3 ሺህ 604 የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ሲሆኑ ፥ 1 ሺህ 883ቱ ሴቶች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version