Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አዲሱ ትውልድ ለውጥ አምጪ እንጂ ያለፉትን ስህተቶች የሚደግም መሆን የለበትም- ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29 ፣2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ)አዲሱ ትውልድ ለውጥ አምጪ እንጂ ያለፉትን ስህተቶች የሚደግም መሆን የለበትም-የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ።
ፕሬዝዳንቷ ይህንን ያሉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ መረሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡
“ዛሬ የምታደርጉት ነገር ሁሉ የነገ የአብሮነት መንገዳችንን የሚጎዳ አለመሆኑን ማረጋገጥ ይጠበቅባችኋል” ያሉት ፕሬዝደንቷ ፥ተመራቂ ተማሪዎች የኢትዮጵያን ወቅታዊ ችግር በሰከነ መንፈስ መገንዘብ እንደሚገባቸው ገልፀዋል።
መንጋቱ አይቀርምና የጠፋውን በመመለስ የወደመውን በማስተካከል ለኢትዮጵያችን የቅርብ ከፍታ መስራት ይገባችኋል ብለዋል በንግግራቸው።
በሃገር ጉዳይ ቆሞ ተመልካች ልንሆን አንችልም፡፡ ኢትዮጵያ ለጊዜው ከገጠማት ፈተና በብልሃት ማላቀቅ ያስፈልጋል ያሉት የዕለቱ የክብር እንግዳ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ።
ተመራቂ ተማሪዎችም በዚህ ረገድ የቀሰማችሁትን ዕውቀት በመጠቀም ኢትዮጵያን ለማሻገር መስራት ይጠበቅባችኋልም ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ፣ በማታ እና በተለያዩ መረሃ ግብሮች 6 ሺህ 163 ተማሪዎቹን ነው ለ72ኛ ጊዜ አስመርቋል።
በምርቃት ስነ-ስርዓቱ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ስራ አመራር ሰብሳቢ እና የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተገኝተዋል።
በሶዶ ለማ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
+4
127,020
People Reached
11,481
Engagements
Boost Post
3.6K
30 Comments
88 Shares
Like
Comment
Share
Exit mobile version