Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ በጀመረችበት ወቅት መመረቃችሁ ድርብ ኃላፊነት እንዲኖርባችሁ አድርጓል -ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ72ኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ከ 6ሺህ በላይ ተማሪዎቹን በዛሬው ዕለት በወዳጅነት ፓርክ አስመርቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ እና የዩኒቨርስቲው አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለተመራቂዎች፣ ለተመራቂ ቤተሰቦችና ለዩኒቨርስቲው መምህራንና ሰራተኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች ባስተላለፉት መልዕክትም÷ ተመራቂዎች ኢትዮጵያ የልጆቿን ሁለንተናዊ ድጋፍና መልካም አስተዋጽኦ በምትሻበት በዚህ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ በጀመረችበት ወቅት መመረቃችሁ ድርብርብ ኃላፊነት እንዲኖርባችሁ አድርጓል ብለዋል።
በመሆኑም በምትሰማሩበት የስራ መስክና የህይወት መንገድ የአገራችሁን፣ የህዝቦቿን ተጠቃሚነት እና ኑሮ መሻሻል ለማረጋገጥ በርትታችሁ ልትሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡
መጪው ጊዜ በመደበኛ ትምህርት ያካበታችሁትን እዉቀት በተግባር ምዕራፍ የምትገልጡበት እንዲሆን እመኛለሁ ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ያኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version