Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ስራ ላይ የዋሉ ቴምብሮች ለዕይታ ቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ከጥንት እስከ ዛሬ ሲያገለግሉ የነበሩ ቴምብሮች ለእይታ ቀረቡ።
የዓለም ፖስታ ህብረት የተመሰረተበት 147ኛ ዓመት በፈጠራ ማገገም (ኢኖቬት ቱ ሪከቨር) በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የተዘጋጀው የቴምብር አውደ ርእይ ከዛሬ ክፍት የሖነ ሲሆን÷ ለሰባት ተከታታይ ቀናትም ለህዝብ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ሃና አርአያስላሴ እንደተናገሩት÷ ድርጅቱ ከ1886 ዓ.ም ጀምሮ የፖስታ አገልግሎትን ጨምሮ የተለያዩ የህዝብ አገልግሎቶችን ሲሰጥ የቆየ አንጋፋ ተቋም ነው።
በዚህ ሂደት የተለያዩ ቴምበሮች አገልግሎት ላይ መዋላቸውን ገልጸው ከጥንት እስከ ዛሬ አገልግሎት ላይ የዋሉ ታሪካዊ ቴምብሮች ከዛሬ ጀምሮ ለህዝብ ለእይታ ክፍት መሆናቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ከ1901 ዓ.ም ጀምሮ የአለም ፖስታ ህብረት አባል ሆና መዝለቋን ጠቁመው÷ የፖስታ አገልግሎት በተለያዩ ፈተናዎች እያለፈ አሁን ላይ ደርሷል ብለዋል።
በዛሬው እለት የአውደ ርእዩን መከፈት ተከትሎ በርካታ ሰዎች ታድመው ታሪካዊዮቹን ቴምብሮች ተመልክተዋል።
ከጥንት አስከ ዛሬ አገልግሎት ላይ የዋሉ ቴምብሮችን ለህዝብ ማሳየት ትልቅ መልእክት እንዳለው ጠቁመው÷ የዓለም ፖስታ ህብረት የተመሰረተበት 147ኛ ዓመት ዘንድሮ በ192 አባል አገራት በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version