አዲስ አበባ፣መስከረም 30፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አባላት ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጎብኝተዋል።
የምክር ቤቱ ልዑክ ኑሯቸውን በለንደን ባደረጉት ኢትዮጵያዊ በአቶ አለባቸው ደሳለኝ መሪነት በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ ይታወቃል።
ይህ ልዑክ ዳያስፖራው ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ በሁለንተናዊ መልኩ ማጠናከር እንዲችል ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር እየተወያየ ሲሆን በቆይታውም የተለያዩ ጉዞዎችና ጉብኝቶችን ያደርጋል።
በዚሁ መሰረት ልዑኩ የኢትዮጵያዊያን የጋራ ፕሮጀክት የሆነውን የሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር ጎብኝቱን እያደረገ ነው።
በቀጣይ የልዑኩ ቆይታ ሌሎች አባላት ፕሮጀክቱን እንደሚጎበኙ መገለፁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!