Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

2ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ዛሬ በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ 2ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር “የሳይበር ደህንነት የጋራ ኃላፊነት! እንወቅ! እንጠንቀቅ!” በሚል መሪ ቃል መከበር መጀመሩን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስም በተለያዩ ስነ-ሥርዓቶች እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስም በተለያዩ ስነ-ሥርዓቶች እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

በዓሉን በዋናነት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በማዘጋጀትና በማስተባበር የሚመራው ሲሆን ÷የተለያዩ ባለድርሻ አካላትም ይሳተፉበታል፡፡

የሳይበር ደህንነት ወር መከበር ዓለማም ”የሳይበር ማህበረሰቡን እና ተቋማትን የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ለማጎልበት የሚያስችል ንቅናቄን በማካሄድና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን የማስጠበቅ ተልዕኮ ማገዝ” መሆኑን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version