አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት የበላይነቴን አስቀጥላለሁ ካልሆነም ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ የሚል የሞኝ ዘፈን እየዘፈነ ነው ሲሉ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ገለጹ።
አቶ ሙስጠፌ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩትት÷ አሸባሪው ህወሓት ሁለት ግልጽ ዓላማዎች አሉት።
አንደኛው ኢትዮጵያ ውስጥ ለእኔ ጥቅም የቆመ መንግሥት መምጣት አለበት የሚል ነው።
እንደአለፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያን እንደፈለኳት የማልዘውራት ከሆነ ደግሞ ትግራይ ትገነጠላለች የሚል አቋም ያራምዳል።
ይህንንም የሽብር ቡድኑ አላማ ከአዘጋጃቸው ሰነዶችና ከተግባሩ መረዳት እንደሚቻል የገለጹት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፥ እነዚህን የአሸባሪ ቡድኑን ዓላማዎች ደግሞ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት በፍጹም የሚቀበሉት አይደለም ብለዋል።
ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ አንድነቷ ተጠብቆና ሰላሟ ሰፍኖ እንድትቀጥል ከተፈለገ በእኔ እምነት አሸባሪው ህወሓት መወገድ አለበት ነው ያሉት።
በአሁኑ ጊዜ የህወሓት 27 ዓመታት የግፍ አገዛዝ ስርዓት እንዲቀጥል የሚፈልግ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሌለ ገልጸው፤ ትግራይን እገነጥላለሁ የሚለው ዓላማውም ከውጭ ኃይል ጋር ተባብሮ ኢትዮጵያን የማፍረስ ተላላኪነቱን የሚያረጋግጥ ማሳያ በመሆኑ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት እንደማይፈቅድለት ተናግረዋል።
ሁለቱም ዓላማዎቹ በኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት በኩል ተቀባይነት ማግኘት ስለማይችሉና ከኢትዮጵያውያን ፍላጎት ውጪ ስለሆነ አሸባሪው የህወሓት ቡድን መወገድ አለበት ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!