Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ባለስልጣኑ ከአፍሪካን ፓርክስ ኔትዎርክ ጋር የ5 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ከአፍሪካን ፓርክስ ኔትዎርክ ጋር የ5 ሚሊየን ዶላር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሙን አስታወቀ።
የአፍሪካን ፓርክስ ኔትወርክ ችፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፒተር ዊትናይ እንደገለፁት÷ ስምምነቱ የተፈረመው የጋምቤላ እና ኦሞ ፓርኮችን በትብብር ለመስራት ያለመ ነው።
በደቡብ ሱዳን በኩልም የቡማ ብሔራዊ ፓርክን በማቀናጀት የድንበር ተሻጋሪ የተጠናከረ አስተዳደር ለመስራት መታሰቡን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
በሁለቱ ተቋማት የጋራ ትብብር፣ በህግ ማስከበር፣ የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ የማህበረሰብ ልማት፣ ቱሪዝም እና የብዝሃ ሕይወት ልማትና ጥበቃ ስራ ለመስራት መታሰቡ ተገልጿል፡፡
እነዚህንም ተግባራት ለማከናወን በዓመት 5 ሚሊየን ዶላር የሚሆን በጀት በዕቅድ መያዙን ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ባለፈው ዕረቡ እለት ተመሳሳይ ፊርማ ከደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ጋር መፈራረማቸውንም ጠቁመዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!
Exit mobile version