Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኀብረት ስራ ቤተሰቦች በአማራና አፋር ክልል ለሚገኙ ተፈናቃዮች የመጀመሪያ ዙር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኀብረት ስራ ቤተሰቦች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በአማራና አፋር ክልሎች ለሚገኙ ወገኖች 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚገመቱ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የኀብረት ስራ ቤተሰቦች ድጋፉ ያደረጉት አልባሳት፣ ምግብ፣ የመገልገያና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች መሆኑ ታውቋል፡፡

በአማራ በሰሜን ወሎ የተፈናቀሉ ወገኖች በሚገኙበት ውርጌሳ ከተማ በመገኘት ድጋፋን ያስረከቡት በኢትዮጵያ ኀብረት ስራ ኮሚሽነር አማካሪ አቶ ዳሬቦ ቡሴር ÷እኛ ኢትዮጵያውያን በችግር ጊዜ መረዳዳትና ለሀገራችን ክብር በጋራ መቆም ባህላችን ብቻ ሳይሆን የህልውናችን ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

በመጠለያ ያሉትን ወገኖችን ማየታችንም ለሁለተኛ ዙር ድጋፋ ለማስተባበር ትኩረት እንድንሰጥ አድርጎናል ማለታቸውን ከፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ወልደትንሳይ መኮንን በበኩላቸው ÷ለድጋፉ ምስጋና አቅርበው ብዙ ተፈናቃዮች መኖራቸውን በማመላከት ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version