Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ አዲስ አበባ እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።

የሕብረቱ ኮሚሽን የሚያዘጋጀው የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ጥቅምት 4 እና 5 ቀን 2014 ዓ.ም በአፍሪካ ሕብረት ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ይካሄዳል።

በስብሰባው ለመሳተፍ የላይቤሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲ-ማክስዌል ሳህ ኬማያ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፕሮቶኮል ዋና ሹም አቶ ፈይሰል ዓሊ እና ሌሎች የሚኒስቴሩ የስራ ሃላፊዎች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የሕብረቱ 55 አባል አገራት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

የምክር ቤቱ ስብሰባ የአገራት መሪዎች፣ የአፍሪካ ሕብረት ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማኀበረሰብ ተቋማትና በሕብረቱ ስር የሚገኙ ተቋማት የሚያደርጉት በሶስተኛው አጋማሽ ዓመት ለሚያደርጉት ጥምር ውይይት አጀንዳዎች የሚቀርቡበት ነው።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version