አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ “አጎዋ”ን ከኢትዮጵያ ለማቀብ ያሳየችው ፍላጎት በበርካታ ኢትዮጵያውያን ሕልውና ላይ ያነጣጠረ ነው ሲሉ የሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ሰራተኞች ተናገሩ፡፡
የሃገር ውስጥና የውጭ ጋዜጠኞች በሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡
በፓርኩ እየሰሩ ከሚገኙ አምራች ጉባንያዎችና ሰራተኞች ጋርም ቆይታ አድርገዋል፡፡
በሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ናሳ ጋርመንት የሁለት ሼዶችስራ አስኪያጅ የሆኑት ራግቨንድራ ፓታር አጎዋን ከኢትዮጵያ ለማቀብ የሚደረገው ጥረት በፓርክ ውስጥ ያሉ ሰራተኞችን፣ ከውጭ ለማምረት ወደ ኢትዮጵያ የመጣን አምራችና የሃገር ኢኮኖሚን የሚጎዳ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በስሩ 1 ሺህ 400 ሰራተኞች ያሉት የናሳ ጋርመንት 98 በመቶ የሚሆነው ምርቱን ወደ አሜሪካ ነው የሚልከው፡፡
ስለዚህም አሜሪካ አጎዋን ከኢትዮጵያ የማቀብ እንቅስቃሴዋን እንደምታጤንና ተፈፃሚ እንደማይሆን ያላቸውን እምነት ገልፀው የኢትዮጵያ መንግስትም ዕቀባው ተግባራዊ እንዳይሆን የጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
ሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ 23 ድርጅቶችና 52 የማምረቻ ሼዶች ሲኖሩት ለ35 ሺህ ሰዎች የስራ ዕድል ፈጥሯል፡፡
በፍሬህይወት ሰፊው
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!