Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጥራት ጉድለት ያለባቸው ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታገዱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ደረጃን ያላሟሉ ገቢ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መታገዳቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሦስት ወራት ገቢ ምርቶች ላይ በተደረገ የላብራቶሪ ፍተሻ እና የኢንስፔክሽን ስራ ከደረጃ በታች ሆነው በተገኙ ገቢ ምርቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የወጪና የገቢ እቃዎች የጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ገልጿል፡፡

እርምጃ የተወሰደባቸው ገቢ ምርቶችም 3 ነጥብ 5 ሜትሪክ ቶን (ኤል ኢ ዲ) አምፑል፣ 25 ነጥብ 8 ሜትሪክ ቶን የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ፣ 3ሺህ 688ካርቶን (368 ሺህ 800 ፍሬ) መጠን ያለው የሀይል አባካኝ አምፖል፣ ዘጠኝ ካርቶን የታሸገ ወተት፣ 55 ነጥብ 3 ሜትሪክ ቶን የአተር ክክ፣ 10 ነጥብ 4 ሜትሪክ ቶን ሩዝና 693 ነጥብ 8 ቶን ቀይ ሽንኩርት መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ሚኒስቴሩ በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በ600 ሺህ ሜትሪክ ቶን ገቢ ምርቶች ላይ የኢንስፔክሸን ሥራ ለማከናወን አቅዶ በ586 ሺህ 746 ነጥብ 8 ሜትሪክ ቶን የገቢ ዕቃዎች ላይ የኢንስፔክሽን ሥራ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version