አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በሰሜኑ ጦርነት ለተፈናቀሉ እና በደሴ ከተማ መጠለያ ለሚገኙ ወገኖች 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገች፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ መመሪያ ሰጭነት በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ ተፈናቅለው በደሴ ከተማ መጠለያ ለሚገኙ ወገኖች በሀገረ ስብከቱ ከገዳማት እና አድባራት እንዲሁም በኢትዮ-በርኖስ ሆቴል አማካኝነት ከማኅበረሰቡ የተሰባሰበ 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ ተደርጓል፡፡
አልባሳት፣ ፍራሽ፣ ብርድ ልብስ እና አልሚ ምግቦችን ያካተተው የሀገረ ስብከቱ ድጋፍ ዛሬ በደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ርክክብ ተደርጓል፡፡
ድጋፉን ያስረከቡት የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መጋቢ ሀዲስ ነቅዐ ጥበብ አባቡ መላዉ ኢትዮጵያዉያን ሀገራችን አሁን ላይ ችግር ላይ ናት፤ ተባብረን ልናክማት ይገባል ብለዋል፡፡
በአሸባሪው ቡድን ከቀያቸዉ ተፈናቅለዉ የሚንገላቱትን ወገኖች ልንደርስላቸዉ እና ልንደግፋቸዉ ይገባልም ብለዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ተወካይ አቶ ትዛዙ እንግዳ በበኩላቸዉ÷ ለተደረገዉ ድጋፍ ምሥጋና አቅርበዉ ለተፈናቃዮቹ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ ቦታዉ ድረስ መጥቶ አይዟችሁ ማለትም ስንቅ ነዉ ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!