አዲስ አበባ፣ጥቅምት 3፣2014 (ኤፍ ቢሲ)በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል የተከፈተው የኩላሊት እጥበት ማእከል ለበርካታ ህሙማን አገልግሎቱን በመስጠት ላይ መሆኑ ተገለጸ።
ሆስፒታሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚሰጠውን የህክምና አገልግሎቶችን እየሳደገ እንደሚገኝም አስታውቋል።
በ2009 አመት በውስን የህክምና ክፍሎች አገልግሎት መስጠት የጀመረው የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሼክ ሀሰን የበሬ ሪፈራል ሆስፒታል፥ በአሁኑ ጊዜ በ30 የህክምና ክፍሎችና ዩኒቶች አማካኝነት ከክልሉና ከተለያዩ አጎራባች አከካባቢዎች ለሚመጡ ነዋሪዎች የተለያዩ የህክምና አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል።
በሪፈራል ሆስፒታሉ ከሚሰጡ የህክምና አገልግሎቶች አንዱ በቅርቡ ለአገልግሎት የበቃው የኩላሊት እጥበት( ዲያሊስስ) ማእከል ሲሆን፥ ማእከሉ በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ አካባቢዎች ለሚመጡ የኩላሊት ህሙማን የኩላሊት እጥበት አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ ላይ ነው።
በዲያሊስስ ማእከሉ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑ የኩላሊት ህሙማን ቀደም ሲል በክልሉ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት መስጫ ማእከል ባለመኖሩ አገልግሎቱን ለማግኘት ለከፍተኛ ወጪና እንግልት መዳረጋቸውን አስታውሰው፥ አሁን ግን በሆስፒታሉ በቅርበት በዝቅተኛ ዋጋ የኩላሊት አጥበት አገልግሎት ለማግኘት መቻላቸውን ገልፀዋል።
ሪፈራል ሆስፒታሉ የሚሰጠውን የህክምና አገልግሎቶችን እያሳደገ እንደሚገኝ የገለፁት የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሼክ ሀሰን የበሬ ሪፈራል ሆስፒታል የነርሲንግና ሚድዋይፈሪ አገልግሎት ሀላፊ ዶ/ር ሙክተር አረብ፥ በተለይም በሆስፒታሉ የተከፈተው የኩላሊት እጥበት ማእከል የሆስፒታሉ አገልግሎት አሰጣጥ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ ነው ብለዋል።
ሆስፒታሉ ከክልሉ በተጨማሪ ከተለያዩ አጎራባች አከባቢዎች ለሚመጡ ነዋሪዎች የተለያዩ የህክምና አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ሀላፊው ተናግረዋል።
በቀጣይም አዳዲስ የህክምና ማእከላትን በመክፈት ለተገልጋዩ ህብረተሰብ የሚሰጠውን አገልግሎቶች ለማስፋፋትና ለማሳደግ እቅድ መያዙን ሀላፊው መግለጻቸውን ከክልሉ ብዚሃን መገናኛ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share