አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት ለሕዝብ የገባውን ቃል ወደ መሬት ሊያወርደው እንደሚገባ መጋቤ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ ገለፁ።
የተፎካካሪ ፓርቲዎች በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነቶች ውስጥ መካተታቸዉ ተስፋ ሰጪ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አሕመድ እንዲሁም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በበዓለ ሲመቱ ወቅት ያደረጉት ንግግር መልካም እንደሆነ የጠቆሙት መጋቤ ሀዲስ እሸቱ ቃላቸውን ወደ መሬት እንዲያወርዱትም ጠይቀዋል።
ፓርላማ ላይ የሚደረጉ ንግግሮች መሬት ላይ እስከ ቀበሌ ድረስ መፈፀም ካልቻሉ ብዙ ትርጉም የላቸዉም፤ ቃላቸው በተግባር ላይ ከዋለ ግን ብዙ ለውጦች ማምጣት ይቻላል ያሉት መጋቢ ሀዲስ እሸቱ የኛን አገር ዲሞክራሲ በአውሮፓ ልክ ተቀዶ እንዲሰፋ መጠበቅ አያስፈልግም፤ ጅምሩ ጥሩ ነው፤የተፎካካሪ ፓርቲዎች በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነቶች ውስጥ መካተት ተስፋ ሰጪ ማለታቸዉን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!