አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ በህዋ ሳይንስ ያላትን አቅም እንድትጠቀም በትኩረት መስራት ይገባል ሲሉ የህብረቱ የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ሳራ አንያንግ አግቦር ተናገሩ።
የአፍሪካ ህብረት አህጉሪቷ ላልተጠቀመችበት የህዋ ሳይንስና ለፓን አፍሪካ ሀሳቦች ቅድሚያ ሰጥቶ እደሚሠራ ጠቁመው÷አፍሪካ ከፍተኛ አቅም ቢኖራትም አሁንም የኋላ ቀርነት ምሳሌ መሆኗ ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡
አፍሪካ ያልተነካ ጥሬ እቃና የሰው ሀይል አላት ያሉት ኮሚሽነሯ÷ በተለይም የአጀንዳ 2063 አካል የሆነውን የህዋ ሳይንስ ተሳትፎዋን ለማሳደግ ትሰራለች ብለዋል፡፡
የሰው ሀብቷ በማሰልጠን እንድትጠቀምበት ለማድረግ ይሰራልም ነው ያሉት።
በተጨማሪም መንግስታት ለአፍሪካ ትስስር አህጉር በቀል እውቀቶች ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራልም ብለዋል።
ኮሚሽነሯ በመካሄድ ላይ ካለው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚዎች ስብሰባ ጎን ለጎን ስልጠና ሰጥተዋል።
በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!