አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የዋግ ልማት ማኅበር በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ50 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገለጸ።
የማህበሩ የአዲስ አበባና አካባቢዋ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ምትኩ በየነ በህግ ማስከበር ዘመቻው ምክንያት አርሶ አደሩ ማረስ ባለመቻሉ ሕዝቡ በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በርካታ ሕዝብም በባሕርዳር፣ እብናት፣ ሰሃላ እና ደሴ አካባቢዎች ተጠልሎ እንደሚገኛ እና በየአካባቢው ሕዝብ እና በተለያዩ ተቋማት ድጋፍ እየተደረገለት እንደሆነ ተናገረዋል።
የዋግ ልማት ማኅበር በአዲስ አበባና አካባቢዋ በሚገኙ አባላቱ አማካኝነት ከ50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ማሰባሰቡንና ወደየ አካባቢዎቹ መላኩን አመላክተዋል።
1 ነጥብ 7 ሚሊየን ብሩ በጥሬ ገንዘብ የተሰበሰበ ሲሆን ÷97 በመቶ የሚሆነው ድጋፍ በአይነት የተሰበሰበ እንደሆነ መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!