አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1496ኛው የመውሊድ በዓል በሀረር ከተማ በተለያዩ አድባሮች በተለይም በጀጐል በሮች አንዱ በሆነው ሸዋ በር አካባቢ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯ፡፡
በበዓሉም የተለያዩ የቁርአን ክፍሎች ተነበዋል፤ የነብዪ መሐመድ ስራዎችም ተዘክረዋል፡፡
ነብዩን የሚያወድሱ እና የሚያሞግሱ መንፈሳዊ ዝክሪዎችም ቀርበዋል፡፡
የበዓሉ ታዳሚዎች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሰጡት አስተያየት÷ ነብዩ በምድር ላይ በቆዩባቸው ጊዜያት ያከናወኗቸውን በጎ ተግባራት በማከናወን እርስ በርስ በመተሳሰብና በመዋደድ አርአያነታቸውን መከተል ከዚህኛው ትውልድ ይጠበቃል ብለዋል።
በተሾመ ኃይሉ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!