አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮይሻ ኤሌክትሪክ ሃይል ፕሮጀክት ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
በደቡብ ክልል በኦሞ ወንዝ ላይ እየተካሄደ የሚገኘውና ከህዳሴ ግድብ ቀጥሎ በትልቅነት 2ኛ የሆነው የኮይሻ ፕሮጀክት ሰራተኞች 1 ሚሊየን 51 ሺህ ብር ነው ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ያደረጉት።
የመከላከያ ተወካይ የሆኑት ሻለቃ ታመነ ዘመዴ በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ህዝቡ እያደረገ ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍ ለመከላከያ ሰራዊት የሞራል ስንቅ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የሀገራችን ስጋት እስኪወገድ ድረስ ህዝቡ ድጋፉን እንዲያጠናክርና ከመከላከያ ጎን እንዲቆም መልዕክታቸውን አስተላልፈው የኮይሻ ፕሮጀክት ሰራተኞችን አመስግነዋል።
የደቡብ ክልል የመከላከያ ሀብት አሰባሳቢ አብይ ኮሚቴ አባልና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ በበኩላቸው÷በክልሉ የሚኖሩ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ለመከላከያ ሰራዊት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውንም ከክልሉ ኮሙዩኒዩኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

