Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሜሪካ ማዕቀቧን የማታነሳ ከሆነ የዉይይት ቅድመ ሁኔታ ሊኖር አይችልም -የኢራኑ ፕሬዚደንት

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 9፤2014 (ኤፍ ቢሲ)አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችዉን ማዕቀብ የማታነሳ ከሆነ ከቴህራን  የዉይይት ቅድመ ሁኔታ ሊኖር እንደማይችል የኢራኑ ፕሬዚደንት ኢብራሂም ራይሲ ተናገሩ፡፡

በ2015 የተደረሰዉን የኑክሌር  ስምምነትን ለማደስ የሚደረገውን  ድርድር አስመልክተዉ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚደንት አብራሂም ራይሲ፥ አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችዉን ማዕቀብ የማታነሳ ከሆነ ከቴህራን  የዉይይት ቅድመ ሁኔታ ሊኖር እንደማይችል በሃገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል ።

የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ኤንሪኬ ሞራ ባለፈው ሐሙስ ለውይይት ወደ ቴህራን በተጓዙበት ጊዜ ፕሬዚደንት ራይሲ  በጉደዩ  ዙሪያ ተመሳሳይ መልስ ሰጥተዋል።

ሀገራችን ኢራንም ሆነች የመካከለኛዉ ምስራቅ ሀገራት የአሜሪካን ማዕቀብ እና የሚደረጉ ድርድሮችን በተመለከተ አቋማችን ተመሳሳይ ነዉ ብለዋል ፕሬዚደንቱ፡፡

ኢራን በቅርቡ  ወደ ኦስትሪያ ዋና ከተማ እንደምትመለስ እና አሁንም በሰኔ ወር የተጠናቀቁትን ስድስት ዙር ድርድሮች መዝገቦችን በመገምገም ላይ እንደምትገኝ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ባደረጉት ንግግር ገለፀዋል፡፡

አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት በበኩላቸዉ ኢራን ወደ ድርድር እነድትገባ ግፊት ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።

በዶናለድ  ትራምፕ የአስተዳደር ዘመን ከሁለት ዓመታት በላይ አድካሚና አሰልቺ ድርድሮች ከተደረጉ በኋላ አሜሪካ በኢራን ለይ ማቀቦችን ጥላ ነበር፡፡

ቀደም ሲል አሜሪካ  በፕሬዚዳንት ትራምፕ ምክንያት  ከኑክሌር ድርድር  መውጣቷ  የሚታወስ ነዉ፡፡

በሚኪያስ አየለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version