አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደሴ ከተማ ወጣቶች ከ10 በላይ ሬድዮ የያዙ እና መሳሪያ የታጠቁ ሰርጎ ገቦችን በቁጥጥር ስር አውለው ለፖሊስ አስረክበዋል።
የደሴ ከተማ ወጣቶች ተደራጅተው የአካባቢያቸውን ሰላም ለማስጠበቅ እያደረጉት ባለው ጥረት፥ በጢጣ ኬላ ላይ ለቁጥጥር የተሰማሩ ወጣቶች ከ10 በላይ ሬድዮ እና መሳሪያ የያዙ ሰርጎ ገቦችን በቁጥጥር ስር አውለው ለፖሊስ ማስረከባቸው ተገልጿል።
በስፍራው የሚገኙት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች ያነጋገሯቸው ወጣቶች እንደገለጹት፥ ወጣቱ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር በመሆን የከተማዋንና አካባቢውን ጸጥታ በንቃት እየጠበቀ ነው።
በዚህ የወጣቶችና የጸጥታ አካላት ትብብርም ወጣቶች ጢጣ ኬላ ላይ ከ10 በላይ የሆኑና መገናኛ ሬዲዮ የያዙ የታጠቁ ሰርጎ ገቦችን በቁጥጥር ስር ማዋለቸውን የወጣቶቹ አስተባባሪ የሆነው ወጣት ጀማል ካሳ ተናግሯል።
ወጣት ጀማል እንደተናገረው ፥ ወጣቱ አስቀድሞ ስልጠና እንደተሰጠው እና በስልጠናውም መሰረት በከተማዋ ወሳኝ በሚባሉ ቦታዎች ላይ ተሰማርቶ ጥበቃ እያደረገ ይገኛል።
ከዚህም ባለፈ የከተማዋ ወጣት ወደ ግንባር እየሄደ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስተባባሪው ገልጿል።
እሱ የሚኖርበት የጢጣ ቀበሌም በቅርቡ 15 ኩንታል በሶ አዘጋጅቶ ወደ ግንባር ለመላክ ዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል።
“ሚስቶቻችንን እና ልጆቻችንን ታቅፈን ቤታችን ቁጭ ብለን አንሞትም ወደ ግንባር ሄደን እንዋጋለን” በሚልም ወጣቱ ተግባራዊ እንቅስቃሴውን እያደረገ ይገኛል ብሏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

0
People Reached
142
Engagements
Boost Post
132
5 Comments
5 Shares
Like
Comment
Share