Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፍሪካ አገራት የወጣቶቻቸውን አቅም መጠቀም የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር ይኖርባቸዋል – ሁሪያ አሊ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ አገራት የወጣቶቻቸውን አቅም ለመጠቀም የሚያስችል ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢ ሁኔታ መፍጠር ይኖርባቸዋል ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ሁሪያ አሊ ገለጹ።
7ኛው የአፍሪካ የስራ ፈጠራና ኢኖቬሽን ጉባኤ በበይነ-መረብ ተካሂዷል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ሁሪያ አሊ፥ የአፍሪካ አገራት የወጣቶቻቸውን አቅም ለመጠቀም የሚያስችል ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢ ሁኔታ መፍጠር ይኖርባቸዋል ብለዋል።
አፍሪካ ከ250 ሚሊየን በላይ ወጣቶች አሏት ያሉት ሚኒስትር ዲኤታዋ፥ የዚህን ወጣት አቅም አሟጦ ለመጠቀምና የቴክኖሎጂ መፍትሄ አፍላቂ እንዲሆኑ ለማድረግ መንግስታት በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አብራርተዋል።
በኢትዮጵያ ከፍተኛ የወጣቶች ቁጥር መኖር፣ ተፈትኖ የተረጋገጠ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት፣ የቴክኖሎጂ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በመንግስት በኩል ያለ ቁርጠኝነት በዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን እንደ መልካም አጋጣሚ የተጠቀሱ ናቸው።
በጉባኤው ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ ወጣት የስራ ፈጣሪዎች እና ባለድርሻ አካላት መሳተፋቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version