Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የብልጽግና ፓርቲና የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ግንኙነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋገጡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ እና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዚሀኦ ዚሂኦን በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት ተገናኝተው በኢትዮጵያና በቻይና ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

በብልጽግና ፓርቲና በቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ መካከል ያለው ግንኙነት ስትራቴጂያዊ በሆነ መልኩ በሚያድግበት ጉዳይ ላይ መክረዋል ነው የተባለው፡፡

የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የቻይና መንግስትና ህዝብ ከኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ጎን መቆማቸውን ጠቅሰው ÷ አቶ አደም ፋራህ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ቻይና በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት ጽኑ መርህን በዓለም እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ያልተቋረጠ ጥረትም በእጅጉ በማድነቅ ÷ የቻይና መንግስትና ህዝብ በሁሉም መስኮች ለኢትዮጵያ በሚያደርጉት ድጋፍና ትብብር የብልጽግና ፓርቲ ትልቅ አክብሮት እንዳለውም አንስተዋል፡፡

የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ÷ መንግስትና ህዝብ ከኢትዮጰያ ጎን እንደሚቆሙ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር አረጋግጠዋል፡፡

የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ በቅርቡ ባደረገው ጉባኤም የቻይና እና የአፍሪካ ትብብርን ለማጠናከር አቅጣጫ እንደተቀመጠም አንስተዋል፡፡

በሁለቱ አገራት መካከል የተጀመረውን ግንኙነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እና በቻይና ኮሚኒስት ፓርቲና በብልጽግና ፓርቲ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ለማጎልበት እንደሚሰሩ አምባሳደሩ ማረጋገጣቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version