Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የተቋረጠውን የጅማ አባጅፋር ቤተ መንግስት እድሳት ለማስቀጠል አዲስ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ተቋርጦ የነበረውን የጅማ አባጅፋር ቤተ መንግስት እድሳት ለማስቀጠል አዲስ የስምምነት ሰነድ ተፈርሟል፡፡
 
የቅርስ ጥበቃና ጥናት ባለስልጣን÷ለቤተ መንግሥቱ እድሳት የወጣው ወጪና የተሰራው ስራ አይመጣጠንም በሚል ግንባታው እንዲቋረጥ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
 
ባለ ሥልጣን መስርያ ቤቱ እድሳቱን ለማስቀጠል ዛሬ ከፕላኔት የታሪካዊ ቦታዎችና ህንፃዎች የጥበቃ አገልግሎት ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል።
 
ለእድሳቱ ግንባታ 8 ሚሊየን ብር መመደቡንና በአንድ ዓመት ከአራት ወራት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሁንዴ ከበደ ተናግረዋል።
 
በቅርስና ጥበቃ ባለስልጣን የጥናትና ምርምር ዳይሬክተር አቶ አንዱአለም፥ ከዚህ በፊት የነበሩ ችግሮችን በመቅረፍ የእድሳት ስራው እንዲጀመር መደረጉን ነው የገለጹት፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ግንባታው እስኪጠናቀቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያደርግ ም ነው ያመላከቱት።
 
የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ነጂብ አባ ራያ በበኩላቸው÷ የቤተመንግስቱ እድሳት እስኪጠናቀቅ የከተማው መስተዳድር አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
 
በሙክታር ጠሃ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version