Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአሸባሪዎቹ ሕወሃትና ሸኔ አገር የማፍረስ ጥረት በሕዝቡ የተባበረ ክንድ እየመከነ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪዎቹ ሕወሃትና ሸኔ አገር የማፍረስ ጥረት በሕዝቡ የተባበረ ክንድ እየመከነ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ገለጹ።
 
የቢሮው ሃላፊው አቶ ኃይሉ አዱኛ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ እንዳሉት የአሸባሪዎቹ ሕወሃትና ሸኔ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የቻሉትን ሁሉ ጥረት አድርገዋል።
የሽብር ቡድኑ ሕወሃት ”እኔ ያልመራኋት ኢትዮጵያ ትፍረስ” በሚል ቅዠት የትግራይን ህዝብ ከህፃናት እስከ አዛውንት ለእኩይ ዓላማው ማስፈጸሚያ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
 
በኦሮሞ ሕዝብ ስም የሚነግደውና በከሰረ የፖለቲካ አዙሪት ውስጥ ከወደቀው የሸኔ የሽብር ቡድን ጋር ግንባር ፈጥሮ አገር ለማፍረስ እተፍጨረጨረ መሆኑን አንስተዋል።
 
የሽብር ቡድኑ ሕወሃት ላለፉት 30 አመታት ኢትዮጵያን ሲዘርፍና ሲያዘርፍ የቆየ መሆኑና አሸባሪው ሸኔም የኦሮሞ ሕዝብ ጠላት በመሆኑን ኢትዮጵያውያን በቅጡ ይረዱታል ብለዋል አቶ ኃይሉ።
አሸባሪው ሸኔ የሽብር ቡድን የኦሮሞን ህዝብ እያሳደደ፣ ንብረት እየዘረፈ፣ የኦሮሞን እናቶች እያስለቀሰና እየደፈረ የኖረ የጥፋት ቡድን መሆኑን አንስተዋል።
 
የሽብር ቡድኖቹ የጋራ አላማ ኢትዮጵያን ማፍረስና ኢትዮጵያዊ አንድነትን መበተን ነው ያሉት ሃላፊው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ይህን እኩይ ተግባር ከማውገዝ በተጨማሪ በተባበረ ክንድ እየመከተ መሆኑን ጠቅሰዋል።
 
ኢትዮጵያን ከገጠማት ወቅታዊ ችግር በአጭር ጊዜ ለማላቀቅ መንግሥት እየወሰደ ባለው እርምጃ የጠላት አከርካሪ እየተመታ እደሚገኝ ገልጸዋል።
 
የሽብር ቡድኖቹን ግበዓተ መሬት በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ህዝብና መንግሥት በትብብር እየሰራ መሆኑንም ሃላፊው ገልጸዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version