አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የጎንደር ከተማ ነዋሪዋ እናት ወ/ሮ ታየሽ ከበደ ሁለት ልጆቻቸውን እና ባለቤታቸውን ዘመቻ ሸኝተዋል።
ወ/ሮ ታየሽ አሸባሪውና ወራሪው የህወሓት ቡድን በኢትዮጵያ ላይ በተለይ በአማራና አፋር ክልሎች እያደረገ ያለውን ወረራ ለመመከት ባለቤታቸውን 10 አለቃ ክብረት ደሴ እና ልጆቻቸው ታዘባቸው ክብረት እና ጌታቸው ክብረትን ሀገራችሁንና ህዝባችሁን አድኑ ብየ ልኬያቸዋለሁ ብለዋል።
እኔም አቅሜ የፈቀደውን የስንቅ ዝግጅት እያረኩ እገኛለሁም ነው ያሉት።
የሶስት ልጆች እናት የሆኑ ግለሰቧ ትንሹ ልጀ ገና የ7ኛ ክፍል ተማሪ በመሆኑ ነው ሊዘምት ያልቻለው ብለዋል።
ቀሪው የሀገሪቱ ህዝብ በተለይ ወጣቱ በሌሎች የተወረሩ አካባቢዎች ያሉ ህዝቦች እየደረሰባቸው ያለው ግፍ ነገም በኔ ይደርሳል ብሎ በማሰብ ሊዘምት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
የዘመቱ ቤተሰቦቸ አሸንፈው እንደሚመጡ አልጠራጠርም ያሉት እናት ፥የጀግና ሚስት እና የጀግኖች እናት የሚል ሁለት ማዕረግ ባለቤት በመሆኔ ከፍተኛ ኩራት ይሰማኛል ማህበረሰቡና መንግስትም ከጎኔ አልተለዩም እያበረታቱኝ ነው ብለዋል።
ሀገርን ለማናዳን እኔ ያለኝን ሁሉ ቤተሰቤን ወራሪውን ሀይል እንዲደመስሱ ልኪያለሁ እናንተም ታሪክ የመስሪያ እድል ተሰጥቷችኋል ዝመቱ የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በኤልያስ አንሙት
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

0
People reached
0
Engagements
–
Distribution score
Boost post
Like
Comment
Share