አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይልና ከሚሊሻ አባላት ጋር በመቀናጀት በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የሚንቀሳቀሱ የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ ሰሞኑን የተቀናጀ እርምጃ መውሰዱን የፌደራል ፖሊስ ገለፀ፡፡
በተካሄደው የማጥቃት ዘመቻም በርካታ የኦነግ ሸኔ አባላት መደምሰሳቸውንና አስር ግብረ አበሮቻቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸው እንዲሁም አሸባሪዎቹ በወቅቱ ሲጠቀሙበት የነበረ በርካታ ገንዘብ መያዙ ታውቋል፡፡
የአሸባሪው ህወሓት ጁንታ ቡድን ተላላኪ የሆነው የኦነግ ሸኔ ቡድን በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጮመን ወረዳ በፈጫሰ፣ አየለ፣ ችንቦና በመሳሰሉት ቀበሌዎች የህዝብ ንብረቶችን በማውደም፣ የንፁሃን ዜጎችን ህይወት በማጥፋትና መንገድ በመዝጋት ህብረተሰቡን ለእንግልትና ስቃይ መዳረጉ ታውቋል፡፡
ህብረተሰቡ ለፀጥታ ሀይሉ ባደረሰው ጥቆማ መሰረት አሸባሪ ቡድኑ አረመኔያዊ ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ የተሸሸገበት ሥፍራ በመድረስ በፀጥታ ሀይሉ የተቀናጀ እርምጃ እንደተወሰደበት መገለፁን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በጮመን ወረዳ ገበቴ ከተማ አስር የኦነግ ሸኔ ተባባሪ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው ለህግ እንዲቀርቡ ተደርጓል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

