Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአራት ወራት ከ123 ቢሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአራት ወራት ከ123 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስወቀ፡፡
በ2014 በጀት ዓመት በአራት ወራት 133ቢሊየን 381ሚሊየን 680ሺህ ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ነው 123ቢሊየን 962ሚሊየን 650ሺህ ብር መሰብሰብ የተቻለው፡፡ አፈጻጸሙም 92 ነጥብ 94 በመቶ መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ ያስወቀው፡፡
እቅድ አፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ16 ቢሊየን 334 ሚሊየን 850ሺህ ብር ዕድገት ማሳየቱም ነው የተገለጸው፡፡ ይኸውም 15 ነጥብ 18 በመቶ ዕድገት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ገቢው የተሰበሰበውም ከሀገር ውስጥ ታክስ 80ቢሊየን 846ሚሊየን 400ሺህ ብር እንዲሁም ከውጭ ንግድ ታክስና ቀረጥ 43ቢሊየን 116ሚሊየን 250ሺህ ብር ነው፡፡
ገቢው በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ገቢን ለመሰብሰብ በማይመች ሁኔታ ውስጥ ሆኖ የተሰበሰበ በመሆኑ አፈፃፀሙ የተሻለ ሊባል የሚችል ነው መባሉን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የተመዘገበው ስኬትም÷ ግብር ከፋዮች ለአገራቸውና ለህዝባቸው በማሰብ በወቅቱና በትክክለኛው ጊዜ ግብራቸው አሳውቀው በመክፈላቸው እንዲሁም የሚኒስቴሩ እና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞችም ከምንጊዜውም በላይ የዕረፍት ጊዜአቸውን ጨምረው በቁርጠኝነት እና በትጋት መስራት በመቻላቸው የተገኘ ውጤት ነው ተብሏል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version