Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

“አሸባሪው ሕወሓት በሥልጣን ዘመኑ ሌብነት እንዲስፋፋ አድርጓል” – የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ሕወሓት በሥልጣን ዘመኑ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ላይ ኢ-ፍትሃዊነት እንዲነግስና ሌብነት እንዲስፋፋ በማድረግ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የባንኩ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሐንስ አያሌው ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ÷ይሰጡ የነበሩ ብድሮች በአግባቡ ያልተመሩ እና የተበላሸ የብድር አመላለስ ሂደቶች የሚስተዋልባቸው ብሎም የማይመለሱ ብድሮች ነበሩ ብለዋል፡፡

ባንኩ በገንዘብ ይደግፋቸው የነበሩ ፕሮጀክቶች በአብዛኛው ወደ አንድ ወገን የሚያተኩሩበት ሁኔታ እንደነበር አስታውሰው፣ ሂደቱም በርካታ ፕሮጀክቶች መድረስ በሚገባቸው ደረጃ ላይ እንዳይደርሱ ተጽዕኖ ፈጥሯል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

አቅሙና ሐብቱ ያላቸው ክልሎች ላይ ሊተገበሩ ይገባቸው የነበሩ ፕሮጀክቶች ወደ ሌላ አካባቢ የተዘዋወሩበት ሁኔታ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

Exit mobile version