አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገርን ሉዓላዊነት ማስከበር ለመከላከያ ሠራዊት ብቻ የተሰጠ ሳይሆን የሁላችንም ጉዳይ ነው ሲሉ በአርባ ምንጭ የሃይሌ ሪዞርት ሠራተኞች ገለጹ፡፡
በአርባ ምንጭ ሃይሌ ሪዞርት የሚገኙ 200 ሠራተኞች በዛሬው እለት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከወር ገቢያቸው 100 ሺህ ብር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ 50 ዩኒት ደም ለግሰዋል፡፡
የድርጅቱ ሠራተኞች በወቅቱ ለኢዜአ እንደተናገሩት ፥ አሸባሪው ህወሓት በሀገር መከላከያ ሠራዊትና በንጹሃን ዜጎች ላይ የፈጸመው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በታሪክ የማይረሳ ግፍ ነው፡፡
“እኛ የሰላም አየር መተንፈስ የቻልነው የህዝብ ልጆች የሆኑት የመከላከያ ሠራዊትና ሌሎች የጸጥታ ሃይሎች እየተዋደቁልን በመሆኑ ነዉ” ሲሉ የገለጹት ሰራተኞቹ ፥ “የዜግነት ድርሻችንን ለመወጣት ካለን ትንሽ ገቢ ለሰራዊቱ ድጋፍ አድርገናል” ብለዋል፡፡
አክለውም ÷ የውጭ መገናኛ ብዙሀን በኢትዮጰያ ላይ የሚያሰራጩትን የሀሰት ዘገባ በማውገዝ በርካታ የዉጭ ዜጎች በምዕራባዊያኑ ‘በሬ ወለደ’ ዜናዎች ሳይሸበሩ ወደ ድርጅታቸው በመምጣት እየተስተናገዱ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
“በቅኝ ያልተገዛች ሀገር ዜጎች እንደመሆናችን የውስጥም ሆነ የውጭ ጫናዎች የሚያጠነክሩን እንጂ ወደኋላ የሚያደርጉን አይደሉም” ነው ያሉት፡፡
“በአገር ጉዳይ ቀልድ የለም ፤ የኢትዮጵያ ልጆች ነንና ለየትኛዉም እጅ ጠምዛዥ ሃይል አንንበረከክም” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
“ስንተባበር አቅም እንሆናለን ፤በተባበረ ክንዳችን የኢትዮጵያን ሰላም እናረጋግጣለን” ነው ያሉት የሪዞርቱ ሰራተኞች፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

