አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ከደባርቅ ወደ ጎንደር ከተማ ተጭኖ ሊገባ የነበረ ከ7 ሺህ በላይ ተተኳሽ የብሬንና የክላሽ ጥይት፣ አንድ ክላሽን ኮቭ፣ ልዩ ልዩ የባንክ የሂሳብ ደብተሮች፣ ሲም ካርዶች፣ የብሬን አንገት በደባርቅ ከተማ ተይዟል፡፡
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ከሃገር መከላከያ ሰራዊት ጋር ባደረገዉ የተጠናከረ ክትትል መሳሪያዎቹ መያዛቸውተጠቁሟል ፡፡
በጎንደር ከተማ የቀበሌ 15 ነዋሪ ፍጹም ገብረ ክርስቶስ ÷ በሰሌዳ ቁጥር 03 አማ – 25162 በሆነ ሚስቱቡሽ ፒክ አፕ መኪና ‘ለጸጥታ አካላት የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠሁ ነዉ’ በማለት በተከዜ ግንባር ከሳምንት በላይ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡
ግለሰቡ ወደ ዛሪማ በሚመላለስበት ወቅት የወገንን ሃይል አሰላለፍና የከባድ መሳሪያዎችን አቀማመጥ ለጠላት መረጃ አሳልፎ ሲሰጥ የቆየ እንደነበር ተናግሯል፡፡
አሁንም ከመኪናዋ ሞደፊክ ባሰራዉ የህገ ወጥ እቃዎች መጫኛ ተተኳሾችን ከዛሪማና ከደባርቅ በመሰብሰብ ወደ ጎንደር በመዉሰድ ለቅማንት ጽንፈኛ ቡድን ለማቀበል ስምምነት እንደነበረዉ መናገሩን ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

