Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በምርት ዘመኑ በመኸር ልማት 13 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013/14 የምርት ዘመን በመኸር ልማት 13 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽ አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ፥ በ2013/14 የምርት ዘመን በመኸር ልማት 13 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ የምርት አሰባሰብ ስራው መጀመሩን ያነሱት ሚኒስትር ዲኤታዋ 12 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር መሸፈን መቻሉን ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል በጦርነት ቀጠናው የሚገኙ በተለይም በአማራ ክልል 5 ዞኖች 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ ተዘርቶ እንክብካቤ ያልተደረገለት ሰብል መኖሩንም አንስተዋል፡፡

በእነዚህ ዞኖች ከ74 ሚሊየን በላይ ኩንታል ምርት ተሰብስቧል ያሉት ሚኒስትር ዲኤታዋ፥ ጉድለቱን ለማካካስ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

የምርት አሰባሰቡ ስራ በሰው ሃይል ከመሆኑ ጋር ተያይዞም ብክነትን ለመቀነስ እንዲሁም ቀልጣፋ እንዲሆን 1 ሺህ 200 ኮምባይነሮች ወደ ስራ ገብተዋልም ነው ያሉት ፡፡

የመደበኛ የመስኖ ልማት ስራ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን በመጥቀስም፥ ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በአገር ውስጥ ለመተካት 400 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ 16 ሚሊየን ኩንታል ለማምረት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በማካካሻ ስራ ላይ በመስኖ ስንዴ ልማት 33 ሺህ ሄክታር መሬት ታርሶ እስካሁን 28 ሺህ ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑንም በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡

በፌቨን ቢሻው

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version