አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለመከላከያ ሠራዊት ከ70 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አድርጓል፡፡
ክፍለ ከተማው ያሰባሰበውን ከ70 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ በዛሬው ዕለት ለመከላከያ ሚኒስቴር አስረክቧል፡፡
በርክክብ ስነ ሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ፣ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሽታዬ መሀመድ እንዲሁም የአገር መከላከያ ሰራዊት አመራሮች ተገኝተዋል።
አቶ ጃንጥራር አሸባሪውና ወራሪው ህወሓትን በመጠቀም እንደዳቦ ቆርሰው ሊውጧት የሚቋምጡ ሃይሎችን አሳፍረን ለመመለስ ሁላችንም በአንድነት ተነስተን ለአገራችን ህልውና መፋለም አለብን ማለታቸውን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

