Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለውጭ አገር ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል 23 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት ወራት ለሱዳንና ጅቡቲ ካቀረበችው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 23 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ለሱዳን 263 ነጥብ 7 ሚሊየን ኪሎ ዋት ኃይል ሽጣ 13 ነጥብ 18 ሚሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ ለጅቡቲ ከቀረበው 159 ነጥብ 6 ሚሊየን ኪሎ ዋት ኃይል÷ 9 ነጥብ 76 ሚሊየን ዶላር ተገኝቷል ብለዋል፡፡
ለሁለቱ አገራት ከቀረበው የኤሌክትሪክ ሽያጭ በድምሩ 23 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ገቢ መገኘቱን ነው አቶ ሞገስ የተናገሩት፡፡
ከፍተኛ የሆነ የኤክስፖርት ገቢያችን ባለፈው በጀት ዓመት የተመዘገበ ገቢ መሆኑን ጠቁመው÷ ከ90 ሚሊየን ዶላር ያላነሰ ገቢ ከኤክስፖርት ሽያጭ መገኘቱን አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገራት የምትልከው የኤሌክትሪክ ኃይል የውጭ ምንዛሬ ከማስገኘት ባሻገር ከአገራቱ ጋር ያላትን የኢኮኖሚ ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር እንደሆነም ነው የገለጹት።
አቶ ሞገስ አያይዘውም÷ የታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በግንባታ ላይ ያሉ ሌሎች ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ኢትዮጵያ ለሌሎች አገራት የምታቀርበው የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚጨምር ገልጸዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version