አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳያስፖራው ባለፉት ሦስት ወራት 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ውስጥ መላኩን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ገለጸ።
የኤጀንሲው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን ግርማ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ ከዳያስፖራው ወደ ኢትዮጵያ የሚላከው ገንዘብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።
ለዚህም ዳያስፖራው በ2013 ዓ.ም በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ቤት የላከውን 3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ባለፉት ሦስት ወራት ከተላከው ጋር በማነጻጸር ለአብነት ጠቅሰዋል።
“ባለፉት ሦስት ወራት ወደ 1 ሺህ 400 የሚሆኑ የዳያስፖራ አካውንቶች ተከፍተዋል፥ ከዚህም ውስጥ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ተቀማጭ ሆኗል ብለዋል።
በተጨማሪም እስከ መስከረም መጨረሻ ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ዳያስፖራው በውጭ ምንዛሬ መልክ ወደ አገር ቤት ልኳል።
በሌላ በኩል በተለያዩ የዓለም አገራት የሚገኘው የዳያስፖራ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን የውጭ ጫና ለመከላከል የተለያዩ ጥረቶች እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ከሚያደርጋቸው ተሳትፎዎች ባሻገር በሚኖሩባቸው አገራትም በሠላማዊ ሠልፍ ጭምር እየታገለ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተጓዳኝም ዳያስፖራው ለአገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለሠብዓዊ ድጋፎችና ለዜጎች መልሶ ማቋቋም የገንዘብና የአይነት ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ለአገራዊ ፕሮጀክቶችም ከ251 ሚሊየን ብር በላይ ኃብት ማሰባሰብ እንደተቻለ ጠቁመዋል።
“አይዞን ኢትዮጵያ” የሚል አዲስ ፕላትፎርም በማልማት ወደ ስራ በመገባቱ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ 260 ሺህ ዶላር በላይገንዘብ ማሰባሰብ መቻሉን አቶ ወንድ ወሰን መናገራቸን ኢዜአ ዘግቧል ፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

