አዲስ አበባ ፣ ህዳር 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች በሸዋሮቢት ግንባር በአካል በመገኘት አሸባሪዎችን እየተፋለመ ያለውን ሰራዊት አበረታቱ።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከጀግናው የሀገር መከላከያና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት አሸባሪውን ቡድን የሽብር ሴራውን በማክሸፍ በተለያዩ የጦር ግንባሮች በመፋለም ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ የተመራውና ከፍተኛ አመራሮች የተገኙበት ቡድን በሸዋሮቢት አካባቢ በሚገኙ የፍልሚያ ቀጠናዎች ውስጥ በመዘዋወር ሰራዊቱን አበረታተዋል።
ከፍተኛ አመራሮቹ እንደገለፁት÷ሰራዊቱ ወራሪውን የህወሃትና የሸኔ አሸባሪዎችን ለመፋለምና ለመመከት የሚያስችል ብቁ ቁመና ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በአገር አቀፍ ደረጃ በተቋቋመው ኮማንድ ፖስት የሚመራ የሰሜን፣ የምስራቅ፣ የአድማ ብተና፣ የፀረ-ሽብር እና የፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ አመራርና አባላት በሸዋሮቢት ግንባር መሰማራታቸው ታውቋል።
የአመራሮቹ በግንባር መገኘት መነሳሳትን እንደፈጠረባቸውና ከጀግናው ሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ከክልሉ ልዩ ኃይል፣ ከፀጥታ አካላትና ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመቀናጀት በቂ ዝግጅት አድርገው ጠላትን ድባቅ ለመምታት በከፍተኛ ወኔና ሞራል እንዲንቀሳቀሱ እንዳደረጋቸው ይህንን መረጃ ከስፍራው ያደረሱን የሰራዊቱ አባላት ገልፀዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

