Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አዲሱ የደቡብ ምእራብ ህዝቦች ክልል ምስረታ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአምስቱ ዞኖችና እና ከአንድ ልዩ ወረዳ የተወከሉ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው ምስረታው በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ያለው።
የምዕራቦ ኦሞ ዞን፣ የቤንች ሸኮ ዞን፣ የካፋ ዞን፣ የዳውሮ ዞን እና የሸካ ዞን እንዲሁም የኮንታ ልዩ ወረዳ ህዝቦች በህዝበ ውሳኔ በአንድ ክልል ለመደራጀት መወሰናቸው ይታወሳል።
ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው ምስረታ ላይም የአዲሱ ክልል ረቂቅ ህገመንግስት ይፀድቃል፣ አፈጉባኤ ይመረጣል፣ ርእሰ መስተዳድር ይሰየማል ተብሎ ይጠበቃል።
በሀብታሙ ተክለስላሴ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version