አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ኀይል አገር ለማፍረስ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለመግታት የሸዋ ሕዝብ ከፍተኛ ጀብዱ በመፈጸም አሸባሪውን ኀይል በገባበት እያሳደደ እየቀበረው መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዲኤታ ንጉሡ ጥላሁን ተናግረዋል፡፡
የሸዋ ተራራዎችና ሸለቆዎች የሽብር ኃይሉ መፈንጫ ሳይሆኑ መቀበሪያቸዉ ይሆናሉ ነው ያሉት፡፡
አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ኀይል በ1982 በሸዋ ምድር የገጠመው ጠንካራ በትር ዛሬም አለ ያሉት አቶ ንጉሡ ÷ የሸዋ ሕዝብ ጠላቱን እንዴት መቅጣት እንዳለበት ያውቅበታል ማለታቸውን የዘገበው አሚኮ ነው፡፡
ሊያጠፋ የመጣውን ጠላት አሁን በተጀመረው ጠንካራ አደረጃጀት በገባባቸው ቦታዎች ሁሉ በማሳደድ መቅበር እንደሚገባም ነው ያስረዱት፡፡
ቀዬን ሳይለቁ ትኩረትን ጠላት መምታት ላይ ማድረግ እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡
አሁን ያለው አሸባሪው ወራሪ ኀይል መበታተኑን ያስረዱት ሚኒስትር ዲኤታዉ ÷ ሁሉም በነቂስ በመውጣት ወደ ፊት እንጅ ወደኋላ ላይመለስ በመትመም ጠላት በገባበት እንዳይወጣ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ነው ያሳሰቡት፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!