Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአማራ ክልል ከ500 ሄክታር በላይ የመስኖ መሬት በዘር ተሸፈነ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ከአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ጋር በመተባበር ከ500 ሄክታር በላይ የመሥኖ መሬት በስንዴ ዘር እንዲሸፈን አደረገ፡፡
በአማራ ክልል አሸባሪው ህወሓት ወረራ ባላደረገባቸው አካባቢወች የሚገኙ ዩኒቨርሲቲወች በጥቂቱ 500 ሄክታር የመስኖ ስንዴ ዘርን በማዘራት ምርታማነት ላይ እንደሚሰሩ ስምምነት ተደርሷል፡፡
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተስፋዬ ሽፈራው እንደገለጹት÷ በኢኮኖሚ ልማቱ ላይ ወራሪ ቡድኑ በአማራ ክልል ስድስት ዞኖች ላይ ያደረሰውን የሠብል ምርት ውድመት ለመሸፈን ዩኒቨርሲቲወች ተሣታፊ መሆን አለብን ብለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው የአፈር ምርምር የውሀ እና የሠብል ባለሙያወችን በመመደብ÷ በምእራብ ጎጃም ዞን በሰሜን ሜጫ ወረዳ አዲስ ልደት ቀበሌ በ502 ሄክታር መሬት ላይ እየሠራ ነው ተብሏል፡፡
በዚህም ለአርሶ አደሮቹ የዘር አቅርቦት እና የማዳበሪያ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን÷ አርሶ አደሮች በጉልበታቸውና በመሬታቸው ላይ አበረታች ስራ እየሠሩ ይገኛሉ፡፡
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ እየደገፈው ባለው የምእራብ ጎጃም ዞን በበጀት አመቱ በዳግም ልማት 91 ሺህ 950 ሄክታር መሬት ለማልማትና 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዶ 95 በመቶ የእርሻ ስራ ተሰርቷል፡፡
በመስኖ ልማት 32 ሺህ ሄክታር መሬት በማልማት 6 ነጥብ 9 ሚሊየን ኩንታል ለማምረት ታቅዶ 43 በመቶ መሸፈኑን የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶጥላሁን አለምነህ ገልጸዋል፡፡
በአለባቸው አባተ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version